Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው በአፋር ኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ በኩል በንጹሃን ላይ ጥቃት ፈጸመ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በራህሌ ወረዳ ዓላ ቀበሌ ዓሳ’ዳ የተባለ ቦታ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

ጥቃቱን ለመመከት የአፋር ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ተገቢውን ምላሽ በመስጠታቸው ቡድኑ መሳሪያውን ጥሎ ሸሽቶ ነበር።
ይሁን እንጅ በዛሬው ዕለት ንጋት 11 ሰአት ላይ ድጋሚ ወረራ በማካሄድ ወደ አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ሴቶችና ህፃናት ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ይሁንና ጀግኖቹ የአፋር ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ዛሬም ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ወረራውን የመመከት ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉም ነው ያለው።

አሸባሪው ህወሓት የአፋርን መሬት ለመቀራመት እና ወደ ትግራይ ክልል ለማካለል፥ ብሎም ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ያለውን የረጅም ጊዜ ህልም ለማሳካት የአፋርን ህዝብ በመውረር ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ማድረሱ ይታወቃል።

ጁንታው በሌሊት ወደ ክልሉ ሰርጎ በመግባት ህፃናትን፣ አዛውንቶችንና ሴቶችን ያለምንም ርህራሄ ዘግናኝ ጭፍጭፋ መፈጸሙንም መረጃው አመላክቷል።

በዚህም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮችን ከቀያቸው አፈናቅሎ ለበርካታ ችግሮች ሰለባ አድርጓልም ብሏል።

የሽብር ቡድኑ አሁንም ቀቢፀ ተስፋውን ለመሞከር በተለያዩ አቅጣጫዎች ትንኮሳ የማድረግ ሙከራ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ በአቅራቢያው ከሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር በንቃት በመጠበቅ ሰላሙን እንድያረጋግጥም ጥሪ ቀርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.