Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የደም ናሙና መመርመሪያ እና የደም ዓይነት መለያ ማሽኖች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአይነቱ ለየት ያለ የደም ናሙና መመርመሪያ እና የደም ዓይነት መለያ ማሽን በዛሬው እለት ተመረቀ።

ማሽኑ በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በብሔራዊ ደም ባንክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ በይፋ ተመርቋል።

የማሽኑ መመረቅ ዘመናዊ፣ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የደም ባንክ አገልግሎት መስጠት ያስችላል መባሉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም የደም ተዋጽኦ አሰባሰብ፣ አመራረትና አጠቃቀም ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ያስችላልም ነው የተባለው።

የእነዚህ ማሽኖች መተከል ከዚህ ቀደም በአማካይ ከ3 እስከ 4 ሰዓት ይወስድ የነበረውን 100 የሚደርስ የደም ናሙና ምርመራና የደም ልየታን ወደ አንድ ሰዓት በመቀነስ ከ200 በላይ የሚሆኑ የደም ናሙናዎችን መመርመርና የደም አይነቶችን መለየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ጥራቱን የጠበቀ የደም ምርመራና የደም ልየታን ያለምንም እንከን ከማከናወናቸውም በተጨማሪ ከሰው ንክኪ የጸዳና በቀላሉ በአንድና በሁለት ሰው ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ መሆናቸውም ተገልጿል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አምስት ከተሞች አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ እና ጅግጅጋ የተተከሉት ማሽኞች በዋናነት 24 የደም ባንክ ቅርንጫፎችን በማስተሳሰር አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.