የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደለም – ዶክተር አብርሃም በላይ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አለመሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በቦሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ደም በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለራሱ ጥቅም ሲል ብቻ ህፃናትን ከመማገድ ጀምሮ የጦር ወንጀል እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አለመሆኑን በመጥቀስም፥ የአሸባሪው ቡድን ድርጊት የትግራይን ህዝብ ባህል፣ ታሪክ እና እምነት የማይመጥን እና የማይወክል መሆኑን አውስተዋል።
የትግራይ ህዝብ ሁልጊዜም ለኢትዮጵያ አንድነትና ልማት የሚቆም ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም፥ አሸባሪው ህወሓት የህዝቡን ማንነትና ባህል እረስቷልም ብለዋል።
“በአዲስ አበባ የምንገኝ ተጋሩዎች ዛሬ ደም በመለገስ ከመከላከያ ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን” ሲሉ ገልጸዋል።
በዘመን በየነ