የኢንዱስትሪ ቁጥጥር ሥርዓቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት 41 በመቶ መጨመሩ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ክላሮቲ የተሰኘው በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የሳይበር ደህንነት ድጋፍ ሰጪ ዛሬ ባወጣው ዘገባ መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት የኢንዱስትሪ ቁጥጥር ሥርዓቶችን የሚጎዱ ተጋላጭነቶች 41 በመቶ ማደጉን ይፋ አድርጓል።
‘ክላሮቲ’ በ2020 የመጨረሻ አጋማሽ ላይ 449 የሳይበር ደህነንት ተጋላጭነቶች እንደነበር በሪፖርቱ ጠቁሟል።
ሆኖም ይህ ቁጥር በ 2021 የመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ ከ600 በላይ የኢንዱስትሪ ቁጥጥር ሥርዓቶች ተጋላጭነቶች መከሰታቸዉን እና 76 በሚሆኑ የኢንደስትሪ ምርት አቅራቢዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቁሟል።
ተመራማሪዎች የተጋላጭነት ቁጥር ካለፉት ሁለት አመታት አንጻር የተተነተኑ ሲሆን፥ በ2021 ስድስት ወራት የተከሰቱ ተጋላጭነቶች መጠን በ2020 ከተከሰቱ አጠቃላይ ተጋላጭነቶች 25 በመቶ እንደሚልቅ እና ከ2019 ጋር ሲንጻጸር ደግሞ 33 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
አብዛኛዎቹ ይፋ የሆኑ ተጋላጭነቶች ለኢንዱስትሪ ቁጥጥር ስርዓቶች ከባድ አደጋን የደቀኑ መሆናችዉን የጠቆመዉ የክላሮቲ ሪፖርት ፥ከእነዚህ መካከልም 71 ከመቶዎቹ ከፍተኛ አደጋን የደቀኑ ወይም ወሳኝ ተጋላጭነት በሚል ተመድበዋል።
ተመራማሪዎቹ 81 በመቶ የሚሆኑ የጥቃት ተጋላጭነቶች በተጎጂዉ አካል ያልተለዩ ሲሆን፥ በሌሎች ተመራማሪዎች ፣ ምሁራን ፣ የሶስተኛ ወገን ኩባንያዎች እና የምርምር ቡድኖች አማካኝነት የተለዩ መሆናቸዉን ሪፖርቱ ጠቁሟል ሲል ኢመደኤ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!