Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በቶኪዮ ፓራ ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው ልዑክ ሽኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ ፓራ ኦሊምፒክ ተሳትፎ አስፈላጊውን መመዘኛ ላሟሉ የኢትዮጵያ ቡድን አባላት ሽኝት አደረጉ።

ፕሬዚዳንቷ የአካል ጉዳተኛ መሆን ማነስ ያለመሆኑን ጠቅሰው የሀገራቸው ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጉ ዘንድ መልካሙን ተመኝተውላቸዋል።

ኢትዮጵያ በፓራ ኦሊምፒክ ውድድር መሳተፍ የሚችሉ በርካታ ዜጎች እንዳሏት የጠቀሱት ተወዳዳሪዎቹ መመዘኛውን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከታቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የእነርሱ ተሳትፎ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አካል ጉዳተኝነት የተሻለ ግንዛቤና ትኩረት እንዲያገኝ በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል ብለዋል::

የኢትዮጵያ የፓራ ኦሊምፒክ አባላት በመጪው ቅዳሜ ወደ ቶኪዮ እንደሚያመሩ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.