Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ተወላጆች እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ በአዲስ አበባ ደም ለገሱ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ተወላጆች እና የትግራይ ማህበረሰብ ለመከላከያ ሰራዊቱ በአዲስ አበባ የደም ልገሳ አካሂደዋል፡፡

በተለያዪ ግንባሮች እየተዋደቀ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊቱ አስፈላጊውን ድ ጋፍ እያደረጉ መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡

አሸባሪው ህወሀት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ትርጉም አልባ ጦርነት ውስጥ ገብቷል ያሉ ሲሆን ÷ ለዚህ ደግሞ ህፃናትን እና ወጣቶችን ወደ ውጊያ በማስገባት ትግራይ ተተኪ ትውልድ አልባ እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል፡፡

የትግራይ ማህበረሰብ የጁንታውን ድርጊት በእጅጉ እንደሚወግዝም ነው በመርሃ ግብሩ ላይ የተናገሩት፡፡

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚሆን የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

ድጋፍም በሌሎች ዘርፎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.