Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 7 ሺህ 711 መድረሱን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 170 መድረሱንም ነው የገለጸው።

የቫይረሱ ስርጭትም በመላው ቻይና መስፋፋቱን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

የዓለም የጤና ድርጅትም ቫይረሱ ዓለም አቀፍ ስጋት መሆን አለመሆኑን በተመለከተ በዛሬው እለት ይመክራል ተብሏል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ባለፉት ቀናት ከሰው ወደ ሰው የታየው የቫይረሱ ስርጭት አሳስቦናል ብለዋል።

ከቻይና ውጭ ያለው የበሽታው ስርጭት በአንጻራዊነት አነስተኛ የሚባል ደረጃ ላይ ቢገኝም በወረርሽኝ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ቫይረሱ ከቻይና ውጭ በ16 ሃገራት የተከሰተ ሲሆን ሃገራትም ቫይረሱን መከላካያ መንገዶችን እየሞከሩ ይገኛል።

አንዳንድ አየር መንገዶችም ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን መሰረዛቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ እና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.