እስከዛሬ ከታዩት ዘረፋዎች ግዙፍ የተባለ የዲጂታል ገንዘብ ዘረፋ ተፈፀመ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የመረጃ ጠላፊዎች እስከዛሬ ከታዩት ዘረፋዎች ግዙፍ የተባለ የዲጂታል ገንዘብ ዘረፋ መፈጸማቸዉ ተሰምቷል፡፡
የመረጃ መንታፊዎች በዲጂታል ገንዘብ ታሪክ በአንድ ጊዜ የተፈጸመ እና ግዙፍ የተባለዉን 600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መዝረፋቸዉ ተነግሯል።
የመረጃ ጠላፊዎች የብሎክቼይን ሳይት በሆነዉ ፖሊ ኔትዎርክ ኮምፒዉተር የስርዓቱን ተጋላጭነት በመጠቀም 600 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸዉን በሺዎች የሚቆጠሩ የኤተር ክሪፕቶ ቶክኖችን እንደመዘበሩ ተነግሯል።
ክሪፕቶ ቶክን የሚስጥራዊ ገንዝብ አይነት ሲሆን ÷ አንድን ንብረት ወይም የተወሰነ አጠቃቀምን የሚወክል እና በብሎክቼይን ላይ የሚቀመጥ ሃብት ነዉ።
ቶክኖች ለኢንቨስትመንት ዓላማዎች ፣ ሃብት ለማከማቸት ወይም ግዢዎችን ለመፈጸም የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ፖሊ ኔትወርክ ላይ የተፈጸመዉ ጠለፋ ኮይንቼክ እና ኤምቲ ጎክስ ባሉ የዲጂታል ገንዘብ ስርአቶች ላይ ከተፈጸሙ የቅርብ ጊዜ የመረጃ ጥሰቶች ጋር ሲነጻጸር በመጠን ግዙፍ ነው ተብሏል።
ከመረጃ ጥቃቱ በኋላ ፖሊ ኔትወርክ ለመረጃ መንታፊዎች በላከዉ መልእክት “እርስዎ የዘረፉት የገንዘብ መጠን ያልተማከለ ፋይናንስ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ነው ብሏል።
በመረጃ ጥቃቱ ዙሪያ በተደረገ የመጀመሪያ ምርመራ አንድ የመረጃ ጠላፊ በውል ጥሪዎች መካከል የተከሰተን ተጋላጭነት እንደተጠቀመ ፖሊ ኔትወርክ ገልጿል።
ፖሊ ኔትወርክ ያልተማከለ ፋይናንስ አቅራቢ ኩባንያ ነው ።
ይህም ተጠቃሚዎች ከአንድ ብሎክቼን ጋር የተሳሰሩ ቶከኖችን ወደ ተለያዩ አውታረ-መረብ እንዲያስተላልፉ የሚያስችላቸዉ ስርአት የፈጠረ መሆኑን ቢቢሲን ጠቅሶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስነብቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን