Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቡራዩ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አመራር እና ሰራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቡራዩ ከተማ ጠቼ አካባቢ አካሄዱ፡፡

“ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በስኬት ለማስቀጠል የተቋሙ ማህበረሰብ በሙሉ ልብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ያኒአ ሰይድመክይ ከዚህ በፊት ተቋሙ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር ማከናወኑን አስታውሰዋል።

በየአካባቢው የተተከሉት ችግኞች መጽደቃቸውን ለማረጋገጥ በተቋሙ ክትትል ማድረጋቸውን ጠቅሰው፥ በቡራዩ አካባቢ ጨቻ የተተከለው ችግኝ እንዲጸድቅ ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚጥል አረጋግጠዋል።

የቡራዩ ከተማ ከንቲባ አቶ ጀግና ግዛቸው በበኩላቸው ተቋሙ በአካባቢው እያደረገ የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ ልማት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይ መርሃ ግብሩ የተካሄደበትን አካባቢ በመዝናኛ ማዕከልነት እንዲያገለግል ለማስቻል እየተሰራ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.