Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለግሱ፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊዎች ናቸው “ደማችን ደሙን ለሚያፈስልን የመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል ነው በፍቃደኝነት የደም የለገሱት።

ፕ/ር አፈወርቅ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የሃገር መከላከያችን ሃገርን ለማስቀጠል እየከፈለ ላለው የህይወት መስዋትነት የደም ልገሳ በማድረግ አጋርነታቸውን በማሳየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፣ በቀጣይም ከመከላከያ ጎን ነኝ ነው ያሉት።

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሠሎሞን ዘሪሁን በበኩላቸው፣ የሃገርን ህልውና ለማስቀጠል እየተዋደቀ ላለው የመከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ በሞባይል በተጀመረው ድጋፍ ማሰባሰብ በተጨማሪ በጦር ሜዳ ሄደን መዋጋት ባንችል እንኳን ሊተካ የሚችለውን ደማችንን በመለገስ አጋርነታችንን ማሳየታችን ያስደስተናል ብለዋል።

ከድሬዳዋ የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች በፍቃደኝነት ደማቸውን የለገሱት።

ተሳታፊዎቹ ከዚህ በተጨማሪም በሞባይል በ6800 ለመከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.