Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ደጀንነትን በሚያሳይ መልኩ በተለያዩ ወረዳዎች  የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

“ለመከላከያችን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን ” በሚል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ነው በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የህብረሰብ ክፍሎች ወደ ግዳጅ ቀጠና የሚላክ ስንቅ በማዘጋጀት ላይ የሚገኙት።

የሀረሪ ከልል ምክር ቤት  አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አዲስአለም በዛብህ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ወረዳዎች ለመከላከያ ሠራዊት እየተካሄደ ያለው የስንቅ ዝግጅት በመጎብኘት አበረታትተዋል።

በስንቅ ማዘጋጀት ስራው ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሃገር መከላከያ ሠራዊት ለሃገር ሉዓላዊነት መከበር የማይተካ ህይወቱን እየሰጠ በመሆኑ አጋርነታችንን ለማሳየት ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም  ግንባር ድረስ በመሄድ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን በተግባር ለማሳየት ዝግጁ ነን ብለዋል።

መከላከያ ሰራዊታችን ብሄራዊ ኩራታችን ነውና ድጋፍ ማድረጋችን  ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.