የኢትዮጵያና የጀርመን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያና እና የጀርመን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያና እና የጀርመን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባው በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በስብሰባው ላይም የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ መሆኑን በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባው የሀገራቱን ትብብር ወደፊት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ እና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ 115 ዓመታትን ማስቆጠራቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።