አየር መንገዱ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ ኦ ኢ ኤም ሰርቪስ ከተሰኘው የአውሮፕላን አካላት አምራችና የጥገና አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ጋር የተፈረመ ሲሆን፥ ለረጅም አመታት የሚቆይ መሆኑን የኩባንያው መረጃ ያመላክታል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው ለአየር መንገዱን ኤ350 ኤር ባስ አውሮፕላኖች መለዋወጫዎችን በማቅረብና የጥገና አገልግሎት በመስጠት ክትትል ያደርጋል፡፡
ይህም የአየር መንገዱን የአገልግሎት ውጤታማነት ለማስቀጠልና እያደገ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱ የኮቪድ19 ተፅዕኖን በመቋቋም ውጤታማነቱን ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
የኦ ኢ ኤም ፕሬዚዳንት ዲዲዬር ግሬንጀር በበኩላቸው፥ የዓለማችን ስመ ጥር ተቋም ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መስራት በመቻላችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!