ስለ ህዝቦች አንድነት እና ህብረት ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል- አቶ አሻድሊ ሃሰን
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስል ህዝቦች አንድነት እና ህብረት ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል አሉ የቤኒሻንጉል ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሃሰን፡፡
በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ምርቃት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ርዕሰ መስተዳደሩ ፥ስል ህዝቦች አንድነት እና ህብረት ሁላችንም በመስራት የሚለያዩንን አካላት በጋራ ልንታገላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ሊለያዩን የሚሞክሩ የውስጥ እና የውጭ ሀይሎችን በጋራ በመታገል ለልማታችን መፋጠን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያ አሻራ ያረፈበት የህዳሴ ግደብ ግንባታ ሂደቱ እና የውሃ ሙሌት አንዳይስተጓጎል ስንሰራ የነበርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል አቶ አሻድሊ ሃሰን፡፡
አቶ ኡመር መሀመድ የአሶሳ ከተማ ከንቲባ እና የዩኒቨርስቲው የስራ አመራር ቦርድ አባል በበኩላቸው ኢትዮጵያዊ ደግነትን እና ታሪክ ሰሪነትን በማስቀጠል ታሪክ ሰሪ ትውልድ እንድትሆኑ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
በተማሪ ወላጆች የተሰጡንን ሀላፊነት አቅም በፈቀድ ተወጥተናል በቀጣይም ይህንኑ አጥናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!