ጠ/ሚ ዐቢይ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ።
መሪዎቹ በሁለትዮሽ እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ለማድረግ በትናንትናው ዕለት አስመራ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድም በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት አስመራ ገብተዋል።