Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በካፍ የውድድር ፈቃድ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በካፍ የውድድር ፈቃድ አግኝቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ በ2021-22 በሚዘጋጀው የአፍሪካ የሴቶች የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን ክለብ ከካፍ የውድድር ፈቃድ አግኝቷል።

ክለቡ በፋይናንስ ፣ ስፖርታዊ  መስፈርት  ፣ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይልና አስተዳዳር እንዲሁም የክለብ ህጋዊነትን የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ  ካፍ በፈረንጆቹ ሐምሌ  2 ቀን 2021 ለፌዴሬሽኑ በፃፈው ደብዳቤ ክለቡ መሳተፍ የሚችል መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሴቶች ኘሪሚየር ሊግ ውድድር ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አዘጋጅነት በሴካፋ ዞን በኬንያ አስተናጋጅነት ከሐምሌ  18 ቀን 2021 ጀምሮ በሚካሄደው የአፍሪካ የሴቶች የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተሳታፊ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህ ውድድር ክለቦች የሚሳተፋት በሊጋቸው ሻምፒዮን በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ካፍ ያስቀመጣቸውን የክለብ ፈቃድ መስፈርቶች አሟልተው  ሲገኙ ነው ተብሏል፡፡

በሴካፋ ዞን ውድድሩ ሻምፒዮን የሚሆነው ቡድን በአፍሪካ የሴቶች የክለኮች ሻምፒዮና ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆን ከኢትዮጵያ እግር ኳሽ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.