የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ለውጥ ጥያቄ በባለስልጣኑ ተቀባይነት አገኘ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበለትን የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ቅያሬ ጥያቄ ተቀበለ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ‘ትግራይ ቴሌቪዥን’ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ጣቢያ ‘ይሓ ቲቪ’ የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳገኘ ባለስልጣኑ ለኢዜአ ገልጿል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለኢዜአ እንዳረጋገጠው የስያሜ ጥያቄው ምላሽ ማግኘቱን ተከትሎ ጣቢያው በቅርብ ቀናት ውስጥ የአየር ስርጭት ይጀምራል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!