የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሰኔ 23 እስከ 25 ድረስ ሲሰጥ የቆየዉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሰላም ተጠናቋል፡፡
የቢሮው የፈተና ዝግጀትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በመዲናዋ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በ175 የመፈተኛ ጣቢያዎች 72 ሺህ 694 ተማሪዎች ፈተና መውሰድዳቸውን ተናግረዋል፡፡
በአንጻሩ ከ1 ሺህ 80 በላይ ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናውን አለመውሰዳቸው ነው የተገለጸው፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም የፀጥታ ችግር በተረጋጋ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡
ለዚህም በከተማ እና በየደረጃዉ የተደራጀዉ ኮማንድ ፖስት ፣ የፀጥታ አካላት ፣ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ ወላጆች ፣ ተማሪዎች እና ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላትን ለነበራቸዉ አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ከትምህርት ቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን