Fana: At a Speed of Life!

በፍሎሪዳ በደረሰ የህንጻ መደርመስ እስካሁን 150 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት በደረሰ የህንጻ መደርመስ አደጋ እስካሁን 150 የሚሆኑ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም፡፡

ባሳለፍነው ሃሙስ በተከሰተው በዚህ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር ዘጠኝ ሲደርስ÷ 150 የሚሆኑት ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል ነው የተባለው፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች በአደጋው የጠፉ ሰዎችን ለማግኘት እና በህይወት ያሉ ዜጎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ተስፋ የተቀናጀ አሰሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡

የአካባቢው አመራሮች የአደጋው መነሻ ምክንያት ሊሆኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የምህንድስና ባለሙያዎችን አሰማርተው እያስጠኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ ለመከላከል በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ዙሪያ እመከሩ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በተለይም የህንፃውን መሰረት፣ የኮንክሪት ሙሌት እና ከመሬት ውስጥ የሚመነጭ ውሃ መኖሩን ለማጥናት እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ ለህንፃው መደርመስ ምክንያቱ በውል አለመታወቁንም ነው የአካባቢው ባለስልጣናት የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.