በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለምርጫው አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለምርጫው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ነገ ለሚካሄደው ምርጫ የድንኳን መትከል እና መሠል ተግባራት በመከናወን ላይ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ለምርጫው የሚሆን የድንኳን ተከላ እና ለምርጫ ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ተግባራቶችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም ከምርጫው ጎን ለጎን “ኢትዮጵያን እናልብሳት!” በሚል ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ለችግኝ መትከያ የሚሆን ጉድጓዶችን በመቆፈር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለከተማ በሁለት የምርጫ ክልል በ121 የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አየተሰራጩ እንደሚገኙ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ለመመልከት ችሏል።
ተጨማሪ የቁሳቁስ ስርጭቱ እሰከ ዛሬ 9:00 ይጠናቀቃልም ነው የተባለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!