“እመርጣለሁ ፤ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ ” በሚል ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ ከ2.8 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን ሰኞ “እመርጣለሁ ፤ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ ” በሚል ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸው ተገለፀ ፡፡
ሀገራዊ ምርጫን ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማቀናጀት ህብረተሰቡ ከምርጫው ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራውን ማኖር እንዳለበት የአዲሰ አበባ ከተማ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጽዮን ተሾመ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ችግኞችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለመትከል ዕቅድ መያዙን ሃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡
ሕብረተሰቡም ለሀገሩ ያለውን ክብርና ፍቅር ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲያረጋግጥ ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!