አብዛኛዎቹ የራንሰምዌር (ቫይረስ) ጥቃት ያስተናገዱ ተቋማት ለዳግም ጥቃት እየተዳረጉ ነዉ- ጥናት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመረጃ መንታፊዎች የተያዘባቸዉን መረጃ ለማስለቀቀ የራንስም ክፍያ ከከፈሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል 80 ከመቶ የሚሆኑት ድርጅቶች ለዳግም ጥቃት መጋለጣቸዉን የሳይበርሰን ጥናት ጠቁሟል
ሳይበርሰን የተሰኘው የሳይበር ደህንነት ምርት አቅራቢ የሆነዉ ተቋም ባካሄደዉ አዲስ ጥናት እንዳመለከተዉ ከሆነ ተቋማቱ ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ የመረጃ መንታፊዎች ጥቃት እንደሚሰነዘርባቸዉ ነዉ ያመለከተዉ።
‘የራንሰም’ ክፍያ መክፈል የቅጅ ወንጀሎችን ከማበረታታት በተጨማሪ እነዚህ ኩባንያዎች በፍጥነት ወደ ተለመደው ንግድ ሥራቸዉ የመመለስ ዋስትና አለመኖሩን ነው ሳይበርሰን የገለጸው።
ከዚህ ባሻገር ወደ ግማሽ የሚጠጉ የጥናቱ ተሳታፊዎች የሳይበር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ድርጅቶች ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ መረጃዉን የማግኘት እድል ቢፈጠርም አንዳንዶቹ ወይም ሁሉም መረጃዎች እንደሚበላሹ ሳይበርሰን በጥናቱ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ይህም በመረጃ መንታፊዎች የሚጠየቁ የመረጃ ማስለቀቂያ ክፍያዎችን መፈጸም ለተቋማቱ በትክክል መረጃዎቻቸዉን እንደሚያስገኝላቸው ዋስትና አለመሆኑን ማሳያ እንደሆነ እና የመረጃ መንታፊዎች በተጎጂው ድርጅት ላይ እንደገና ጥቃት ከመሰንዘር አያግዳቸውም ተብሏል።
ከዚያ ይልቅ የራንሰም ክፍያ መፈጸም የመረጃ መንታፊዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እንዲያደርሱ የሚገፋፋ መሆኑን ሳይበርሰን መጠቆሙን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመሆኑም የራንሰምዌር ጥቃቶችን ቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል የቅድመ መከላከል ስትራቴጂ መኖር ኩባንያዎች ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እና በድርጅቶቹ ላይ ያንዣበቡ የራንሰምዌር ጥቃት እንቅስቃሴዎችን ቀድሞ ለመግታት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!