Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ስታዲየምን ለማደስ የሚያስችል  ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን የአዲስአበባ ስታዲየምን ለማሳደስ እና ኢንተርናሽናል ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ የተፈረመው በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንና ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ ኃ.የተ. የግል ኩባንያ መካከል ነው።

እድሳቱ በቅድሚያ ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶች መሠረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን÷ የመጫወቻ ሜዳው ፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች ፣ የተመልካች መፀዳጃ እና የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ስራዎችን ያካትታል ።

የእድሳቱን ስራውን ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ ኃ.የተ. የግል ኩባንያ በ39 ሚሊየን 644 ሺህ 748 ብር ያሸነፈ ሲሆን÷ በአጭር ጊዜ ውስጥ እድሳቱን አጠናቆ እንደሚያስረከብ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ገልጿል  ።

የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር÷ ስታዲየሙ በቀጣይ ዓመት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ጨምሮ በርካታ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ እድሳቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ ሊጠናቀቅ ይገባል ብለዋል ።

ኮሚሽኑም  እድሳቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ።

የእድሳት ስራው በተሰራው ዲዛይን መሰረት የሚቀጥል ሲሆን ÷በምዕራፍ ሁለት የሚዲያ ክፍሎች ፣ የክብር ቲሪቡን መቀመጫ ፣ የወንበር ገጠማ ፣እና ሌሎች የስታዲየሙ ክፍሎችን የማደስ እና ለአገልግሎት ምቹ እንደሚደረግ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.