ኢንተርናሽናል ዳኛ አቶ ጌታቸው ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለረጅም አመታት ያገለገሉት አቶ ጌታቸው ተከስተ (ቀስቶ) ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
አቶ ጌታቸው ተከስተ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2013ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጥቅምት 21 ቀን 1992 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በኢንተርናሽናል ዳኝነት ፣ በእግር ኳስ የጨዋታ ህግ ኢንስትራክተርነት እና በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ስርዓተ ቀብራቸው ነገ ሰኔ 3 ቀን 2013 ከቀኑ 7 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!