ዘምዘም ባንክ ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን በትናንትነው እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
የባንክ ዋና ቅርንጫፍ – አሊፍ ቅርንጫፍ (ወሎ ሰፈር አካባቢ) ስራ ሲጀምር የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ፣የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ሃጂ ኦማር ኢድሪስ እንዲሁም ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡
የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መሊካ በድሪ፥ የብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በማሟላት ወደ ስራ እንደገባ እና ለባንኩ እዚህ ደረጃ መድረስ አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም ባንኩ ሸሪዓውን የጠበቀና ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የደንበኞቹን ፍላጎትና የረዥም ጊዜ ጥያቄ ለመመለስና ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ባንኩ በላከልን መገልጫ አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!