Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ሲኖቫክ ክትባት ለኮቪድ19 ድንገተኛ ጥቅም እንዲውል እውቅና ተሰጠው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የቻይናው ሲኖቫክ ክትባት ለኮቪድ19 ድንገተኛ ጥቅም እንዲውል እውቅና ሰጠው፡፡

እንደ ድርጅቱ መግለጫ ክትባቱ ምልክት የሚያሳዩትን በ51 በመቶ እንዲሁም ስር የሰደደ ምልክት ያሳዩትን ሙሉ በሙሉ መከላከል ችሏል፡፡

ይሁን እንጅ በአጠቃላይ ውጤታማነቱ ላይ እርግጠኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ የመረጃ ክፍተቶች እንዳሉም ነው ያስታወቀው፡፡

ክትባቱ እውቅና ማግኘቱን ተከትሎም የኮቪድ19 መከላከያ ክትባትን በፍትሃዊነት ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል፡፡

በበርካታ ሃገራት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ይህ ክትባት እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ለሆናቸው ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ልዩነት ይሰጣል፡፡

ክትባቱ በአንዳንድ ሃገራት በተለይም በብራዚል ውጤታማነቱን እንዳሳየ ቢቢሲ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

በብራዚል ደቡባዊ ክፍል በምትገኝ አንድ ከተማ በተደረገ ጥናትም፥ በከተማዋ የሲኖቫክ ክትባትን ለነዋሪዎች ማዳረስ ከተቻለ በኋላ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በ95 በመቶ ቀንሷል ነው የተባለው፡፡

ሲኖቫክ ከሲኖፋርም ቀጥሎ እውቅና ያገኘ ሁለተኛ ቻይና ሰራሽ የኮቪድ19 ክትባት ሆኗል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.