የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድንና ዳሽን ቢራ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድንና ዳሽን ቢራ የአምስት ዓመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አቶ ድረስ ሳህሉና የዳሽን ቢራ የንግድ ክፍል ዳይሬክተር ፓትሪክ ተፈራርመዋል፡፡
በተደረገው ስምምነት መሰረት ባህርዳር ከተማ የእግር ኳስ ቡድን ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ የ78 ሚሊየን ብር ገቢ የሚያገኝ መሆኑን የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አብርሃም ዘሪሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ይህም በቀጣይ አመታት ቡድኑ ጠንካራ የፕሪሜር ሊጉ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል ተብሏል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ስምምነቱ ለክለቡ እድገት የሚኖረው ሚና እጅግ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ኮሜርሻል ዳይሬክተር ፓትሮክ ፕላንኬት በበኩላቸው ዳሽን ቢራ ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት አበክሮ ይሰራል ብለዋል።
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በቅርቡ የፕሪሜርሊጉ አሸናፊ ለሆነው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ ከ106 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ እዳደረገ መግጹ የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!