Fana: At a Speed of Life!

ለኤጀንሲው ተጠሪ የሆኑ የልማት ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከ59 ቢሊየን ብር በላይ አተረፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ተጠሪ የሆኑ የልማት ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከታክስ በፊት 46 ነጥብ 95 ቢሊየን ትርፍ ለማግኘት አቅደው 59 ነጥብ 78 ቢሊየን ብር አተረፉ፡፡
በዚህም የዕቅዱን 127 ነጥብ 3 በመቶ ማሳከት ተችሏል ነው የተባለው፡፡
ትርፉ ድርጅቶቹ በተጠቀሰው ጊዜ 258 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር የሚያወጣ ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ አቅደው 246 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ወይም የዕቅዳቸውን 95 ነጥብ 2 በመቶ ሽያጭ በማከናወናቸው የተገኘ መሆኑ ታውቋል፡፡
ምርትና አገልግሎታቸውን ለውጭ ገበያ ጭምር ያቀረቡ 11 ድርጅቶች በዚሁ ጊዜ ውስጥ 7 ነጥብ 21 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማግኘት አቅደው 5 ነጥብ 66 ቢሊየን ዶላር ወይም የዕቅዳቸውን 78 ነጥብ 5 በመቶ ሊያገኙ ችለዋል ነው የተባለው፡፡
የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ትዕግሥቱ አምሳሉ የልማት ድርጅቶቹ የኮቪድ19 ወረርሽኝንና ሌሎች በርካታ ጫናዎችን ተቋቁመው አፈጻጸማቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደጉ መምጣታቸውን ገልፀው በቀሪው የበጀት ዓመቱ ጊዜም እንዚህን ተግባራት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከሃያ ድርጅቶች ውስጥም በአስራ አንዱ ግምገማ መካሄዱን ከመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.