Fana: At a Speed of Life!

ቴክኖ ካሞን 17 ወደ ገበያ ገብቷል

&nbspአዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቴክኖ ካሞን 17 በዘጋቢ ፊልም ታግዞ ወደ ገበያ መግባቱን ኩባንያው አስታወቀ ::

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዲሱ ትውልድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በለቀቀው አዲሱ የCAMON 17 ተከታታይ ስልክ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ኩባንያው አስታውቋል::

ይህ ፈጠራ የታከለበት ቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ማጠንጠኛውን በሰልፊ ላይ ባደረገ ዘጋቢ ፊልም የተመረቀ ሲሆን ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ዘርፎች ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል::

“The Rise of Selfie” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ዘጋቢ ፊልም ፊልም በማስመረቂያ ፕሮግራሙ ላይ የቀረበ ሲሆን ታዳሚዎቹ በእርግጥም ቴክኖ የዚህን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በተጨባጭ እና በስሜት እየሰራ መሆኑን ስለመገንዘባቸው ድርጅቱ ገልጿል::

አዲሱ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር ክሪስ ኢቫንስ “ሕያው እና በስሜት የተሞላ ምስል ትፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን መልካም ምስል የሚያደርገው ‘እጅግ ግለሰባዊ’ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ቴክኖ በፅኑ ከሚያምንበት እና ከሚታወቅበት ሃሳብ ጋር ይጣጣማል ብለዋል፡፡

የስማርት ስልክ ፅንሰ ሃሳብ ብራንዱ ላይ ሳይሆን ተጠቃሚው ላይ ማውጠንጠን እንዳለበትም ነው የንግድ አምባሳደሯ የጠቆሙት፡፡

የፋሽን ሞዴል የሆኑት ሣራ በፊልሙ ላይ እንዳሉት እንደ ቴክኖ ካሞን 17 ያሉ የሰልፊ ስልኮች ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ምስል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተወዳጅ ፎቶዎችን በማንሳት ምስላቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል::

በተጨማሪም የተሻለ ማንነት እንዲኖር ለማድረግ እዲሁም በደመነብስ ወደተሻለ እኛነት እንድንመጣ ለራሳችን የምንጠቁምበት መንገድ ነው ብለዋል::

ቴክኖ ካሞን 17 ሁልጊዜ “በልባቸው ወጣት” ለሆኑ እና ለአዳዲስ ነገሮች ራሳቸውን ለሚያነሳሱ ተጠቃሚዎች ምልክት ለመሆን የተሰራ ነው ያለው ድርጅቱ፥ ሰዎች ራሳቸውን በይበልጥ ለመግለጽ እንዲችሉ ያስችላቸዋልም ብሏል፡፡

ኮቪድ19 ባስከተለው ተጽዕኖ ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት ሰልፊን ማዘውተራቸው የሰልፊን ተግባር ይበልጥ አስፈላጊ ያደረገው በመሆኑ ጉዳዩን ቴክኖ እና ሌሎች የስልክ አምራቾች በአጽንኦት እንዲያጤኑት አድርጓቸዋል::

በቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ሰዎች ህይወት ያላቸው የሚመስሉ ፎቶዎችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በFHD ስክሪን ላይ በጣም ግልጽ የሆነ ምስልን ማየት እንደሚያስችላቸው ነው የተገለጸው::

ይህ ከፍተኛ ጥራት ያለው ስክሪን ተጠቃሚዎች በቪዲዮ ጥሪዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽነት የሚሰጣቸው ሲሆን ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ጌሞችን መጫወት እንደሚችሉም ነው ኩባንያው የገለጸው፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.