Fana: At a Speed of Life!

በቼክ ሪፐብሊክ የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በቼክ ሪፐብሊክ ኦስትራቫ ከተማ በተካሄደ የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በውድድሩ አትሌት ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር 8 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ ከ47 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚህ ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም የተሳተፉ ሲሆን በወንዶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ሳሙኤል አባተ በ3 ደቂቃ 36 ሰከንድ ከ32 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቋል፡፡
በተመሳሳይ በሴቶችበ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 4 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አትሌት ሂሩት መሸሻ ውድድሩን ሶስተኛ በመሆን ጨርሳለች፡፡
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ውድድሩን ሳታጠናቅቅ ቀርታለች፡፡
በሌላ በኩል በ800 ሜትር ውድድር አትሌት ደርቤ ወልተጂ በ1 ደቂቃ 59 ሰከንድ በ79 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሁለተኝነት ማጠናቀቋን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.