የ26 ሚሊየን ዶላር (ከ1 ቢሊየን ብር በላይ) ባለ እድል ነኝ ያለች ግለሰብ ሎተሪውን በማጠቧ ከጥቅም ውጭ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ26 ሚሊየን ዶላር ወይም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ባለ እድል የሚያደርገውን ሎተሪ መግዛቷ የተገለፀው ግለሰብ የጃክ ፖት ሎተሪ እጣ አሸናፊ የሆችበትን ትኬት በማጠቧ ሎተሪው ከጥቅም ውጭ መሆኑ ተነግሯል።
የጃክ ፖት ሎተሪውን መግዛቷ የተገለፀው ማንነቷ ያልተገለፀው ግልሰብ በሱሪዋ ኪስ አስቀምጣው እንደነበረና ስታጥበው ሎተሪው ሊባላሽ እንደቻለ ተነግሯል።
እጣው የወጣለት የሱፐር ሎቶ ሎተሪ ቁጥሩ ህዳር ወር ላይ ሎስ አንጀለስ ውስጥ መሸጡ እና ግለሰቧ ትኬቱን ስትገዛ በሲሲቲቪ ካሜራ መታየቷን ቢቢሲ ዘግቧል።
ባለዕድሏ በስድስት ወራት ውስጥ ማሳወቅ የነበረባት ቢሆንም የዚህ ትኬት ባለ እድሏ የተሰጠው ጊዜ በትናትናው እለት እስከ ተጠናቀቀበት ወቅት ሳታሳወቅ ቀርታለች።
ነገር ግን ግለሰቧ የስድስት ወራት ቀነ ገደቡ ሊጠናቀቅ አንድ ቀን በቀረበት ወቅት ትኬቱን ወደ ገዛችበት መደብር አምርታ ባለእድል እንደነበረች ትኬቱን ከልብሷ ጋር ማጠቧን ተናግራለች።
አወዳዳሪ አካሉም ግለሰቧ ትኬቱን ስትገዛ የሚያሳየው ቪዲዮ በቂ አይደለም ያለ ሲሆን ባለእድል መሆኗን ለማረጋገጥ ተጨባጭ ነገር ያስፈልጋል ብሏል።
ቪዲዮው ምርመራ ከተካሄደበት በኋላ የተረጋገጠ አሸናፊ ካልመጣ የእጣው ገንዘብ በካሊፎርኒያ ግዛት ለሚገኙ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ይከፋፈላል ተብሏል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን