የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ያስገነባው ዘመናዊ የስልጠና ማእከል ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ያስገነባው ዘመናዊ የስልጠና ማእከል ተመረቀ።
ማእከሉ በዛሬው እለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
ማእከሉ በ1 ሺህ 80 ሜትር ስኩየር መሬት ላይ የተገነባ ዘመናዊ ህንፃ ሲሆን 16 የመማሪያ ክፍሎችንና ከ40 በላይ የመኝታ ክፍሎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና መስጠት እንዲያስችል ዘመኑ የደረሰባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያካተተ መሆኑም ተመልክቷል።
ከዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች መጻደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!