የስፖርቱን ልማት ያሳልጣል የተባለው የስፖርት ፖርታል ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስፖርት መረጃ እድገት እና ለስፖርት ልማት የጎላ ሚና እንዳለው የተገለጸው የስፖርት ፖርታል ተመርቋል።
ፖርታሉ የስፖርቱን ልማት ለማሳለጥና መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገልጿል።
በምርቃቱ ስነስርዓት ላይ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር÷ ሃገራዊ የስፖርት ሪፎርም መምሪያዎች፣ ደንቦች፣ የስፖርት ግንዛቤን ለማጎልበት እና መልዕክቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የስፖርት ፖርታልን ማቋቋም ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በቴክኖሎጂ የታገዘ የስፖርት ተግባራት ለስፖርት ጥናትና ምርምር የጎላ ድርሻ ስለሚኖረው መላው የስፖርት ባለድርሻ አካላት ፖርታሉን የበለጠ ለማጎልበት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት።
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የቴክሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ዲኤተ ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ሲናሞን ጨምሮ በየደረጃ የሚገኙ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች፣የክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ዙሪያም የተለያዩ ኃሳቦች መስጠታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
+3
1,830
People Reached
36
Engagements
Boost Post
41
2 Comments
1 Share
Like
Comment
Share