Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 149 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በፈረንጆቹ 2021 ላጋጠመው የሰብአዊ ቀውስ ድጋፍ የሚውል 149 ሚሊየን ዩሮ መመደቡን አስታወቀ።

የህብረቱ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔች ሉናርቺች እንደተናገሩት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቀጠናው ካጋጠሙ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ የአንበጣ መንጋ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መስፋፋት ባሻገር መጠነ ሰፊ ግጭቶችና መፈናቀሎች ያሉበት ነው።

በዚህም አስቸኳይ የህይወት አድን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የምግብ የመጠለያና የጤና አገልግሎት እገዛ ሊደረግላቸው ይገባል ማለታቸውን ሪሊፍ ዌብን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ አመላክቷል።

በኮሚሽኑ የድጋፍ ድልድል መሰረት ሶማሊያ 45 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ ሱዳን 52 ሚሊየን፣ ኡጋንዳ 32 ሚሊየን እና ጅቡቲ ግማሽ ሚሊየን ዩሮ የተመደበላቸው ሲሆን ቀሪውን ስምንት ሚሊየን ዩሮ ደግሞ በጋራ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝን መከላከል ይውላል ተብሏል።

ኮሚሽነር ሌናርቺች በሰሞኑ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኢትዮጵያ 53 ነጥብ 7 ሚሊየን እና ለደቡብ ሱዳን 43 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ለሰብአዊ ድጋፍ እገዛ እንዲሆናቸው መስጠቱ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.