Fana: At a Speed of Life!

ፓዎር ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዶሃ የኢትጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት በኳታር የሚገኘው ፓዎር ኢንተርናሽናል ሆልድንግ ኩባንያ እና በኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር ተቀራራቢ ዘርፍ በተሰማሩ መስሪያ ቤቶች መካከል የቅድመ ኢንቨስትመንት ስብሰባ ተካሄደ፡፡
ኩባንያው ከተሰማራባቸው መስኮች ጋር ተያይዞ መንግስት ከግል ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት ሊሰራ ከሚችልባቸው ዘርፎች መካከል በባቡር መሰረት ልማት፣ በአቪየሽን፣ በከተማ ሎጅስቲክ፣ በወደብ ልማት፣ በዲጅታል የትራንስፖርት አገልግሎት እና በመንገድ ልማት ዙሪያ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡
የድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ራሜዝ አልክሃያት በኢትዮጵያ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤት ልማት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
በቅርቡም በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማየት ዕቅድ እንዳለቸው ጠቁመዋል፡፡
በኳታር የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያድርጅቱ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገባ ኤምባሲው ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.