Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የሩሲያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሚሰማሩበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሀገሪቱ ባለሃብቶች ጋር በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ በሚያፈሱበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በሴንት ፒተርስበርግ በክልሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና በንግድ ማህበራት አስተባባሪነት “የእድገት አዳዲስ ህግጋት” በሚል በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ነው፡፡

ከተለያዩ 30 የሩሲያ ከተሞች የተውጣጡ የንግድ አካላትን ጨምሮ የመንግስትና የግል ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል፡፡

አምባሳደሩ በንግድና በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ስላለው ምቹ ሁኔታ፣ ከሩሲያ የኢንቨስትመንት ፍላጎት አንጻር በማዕድን፣ በኢነርጂና በእንፎርሜሸን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በማምረቻና በቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንዲሁም በንግድ ልውውጡ ከቡና፣ ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች በተጨማሪ የአበባን ጥራትና ተፈላጊነት በማውሳት በሩሲያ ገበያ በሰፊው በሚገባበት ሁኔታና በቱሪዝም ሰላለው እምቅ ሃብት አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ጉብኝት ላደረጉት የንግድ የልዑካን ቡድን አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ ከውይይቱ ባሻገር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮችና በሴንት ፒተርስበርግ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚወያዩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.