800 የቻይና ኩባንያዎች በታንዛኒያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 800 የቻይና ኩባንያዎች በተለያዩ ዘርፎች በታንዛኒያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ።
በታንዛኒያ የሚገኙ የቻይና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከአዲሷ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ነው ይህ የተገለፀው።
የቻይና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች የታንዛኒያ መንግስት በኢንቨስትመንት እና ለህዝብ በሚያቀርበው ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የቻይና ኩባንያዎቹ በሞባይል ስልክ ኢንዱስትሪ ፣ በጤና ዘርፍ ፣ በተሽከርካሪ ፋብሪካ እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ በታንዛኒያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ያለመ ነው መባሉን ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል።
ከዚህ ባለፈም በታንዛኒያ የትምህርት ዘርፍ ተሳትፎ ለማድረግ እነዚህ የቻይና ኩባንያዎች ፍላጎት አሳይተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!