በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ሽጉጦች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች መያዙን የጎንደር ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ህገወጥ የጦር መሳሪያው የተገኘው በተለምዶ ህዳሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግለሰብ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡
የመኖሪያ ቤቱ ባለቤት ለጊዜው የተሰወሩ ሲሆን ግለሰቧን ለመያዝና የህገወጥ የጦርመሳሪያውን ምንጭ ለማወቅ ፖሊስ እየሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ገልጸዋል።
በሹመት አለማየሁ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን