በመጋቢት ወር ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት ከ107 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጋቢት ወር ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት ከ107 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስላጣን አስታወቀ፡፡
ገቢው በወሩ ወደ ተለያዩ አገራት ከተላከው 27 ሸህ 200 ቶን ቡና መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህም የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ በአንድ ወር ውስጥ ቡናን ልካ አግኝታ የማታውቀው ነው ተብሏል፡፡
ይህም በዋነኝነት ላኪዎች ቡናን በቀጥታ ትስስር ከአቅራቢዎች እና ከአርሶ አደሮች እንዲገዙ የማድረግ ስርዓት ተዘርግቶ የእሴት ሰንሰለቱ እንዲያጥር በመደረጉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስላጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ባለስልጣኑ በቅርቡ የቡና ግብይቱን የሚያሳልጡ የተለያዩ አሰራር ስርዓቶች መዘርጋቱ እና ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለንⵑ