የፌስቡክ መረጃቸው ከተጠለፈባቸው መካከል ከ12 ሺህ በላይ የኢትዮጵያውያን አካውንቶች ይገኛሉ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 (ኤፍ .ቢ.ሲ) በመረጃ መረብ ጠላፊያዎች የፌስቡክ መረጃዎቻቸው ከተጠለፈባቸው 533 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መካከል ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢትዮጵያ መሰረታቸውን ያደረጉ የፌስቡክ አካውንቶች ናቸው ተብሏል።
የመረጃ ጣለፊያዎች ከፌስቡክ የዘረፉት የግለሰቦች መረጃ በነፃ በጠላፊዎች ህዝባዊ ፎረም ላይ እንደሚገኝ ነው ብሌፒንግ ኮምፒዩተር የዘገው።
ይህ የተሰረቀ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠላፊዎች ለአባላቱ መሸጥ የጀመረው ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2020 ጀምሮ ነው ተብሏል።
የተጠለፈው መረጃ በዋነኝነት ተጠቃሚዎች ህዝባዊ ማድረግ የማይፈልጓቸው መረጃዎች መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል።
የተሰረቁ መረጃዎች ዝርዝርም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ስልክ ቁጥር፣ የፌስቡክ መለያ፣ ስም ፣ ፆታ ፣ አድራሻ ፣ የፍቅር ግንኙነት እና የልደት ቀን የሚያመለክቱ ናቸው።
መረጃ ጠላፊዎቹ በተሰረቀበት ወቅት እስከ 30 ሺህ ዶላር በማስከፈል ለሌሎች መረጃ ጠላፊዎች ሲሸጡ እንደነበረ እና አሁን ላይ የ533 ሚሊየን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በነፃ እንዲለቀቅ መደረጉ ተነግሯል።
በዚህም በኢትዮጵያ የ12 ሺህ 753 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የግል መረጃዎች በመረጃ መዝባሪዎቹ እጅ ገብቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!