Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ዋንጫውን ሊያነሳ ችሏል።

በሎዛ አበራ ሁለት ጎሎች 2 ለ 1 ያሸነፉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በውድድር ዘመኑ 46 ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል፡፡

በአስር ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የነበረው ውድድር ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ሎዛ አበራ በ17 ጎሎች የውድድር ዘመኑ ኮከብ ጎል አግቢ መሆን የቻለች ሲሆን፣ ሌላዋ የቡድኑ ተጫዋች ረሂማ ዘርጋው በ16 ጎሎች ሁለተኛ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን በተጨማሪ የውድድር ዘመኑ ኮከብ ተጫዋች ተብላ መመረጧን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ የቡድኑ አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛውም ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጧል፡፡

የውድድር ዘመኑን መከላከያ 2ኛ ደረጃ ፣ ሀዋሳ ከተማ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ፤ አዲስ አበባ ከተማ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫን አግኝቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.