ካለፈው የጋራ ታሪካችን የወረስናቸውን የተዛቡ ግንኙነቶች በማረም አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሠብ መገንባት ይጠበቅብናል – ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ካለፈው የጋራ ታሪካችን የወረስናቸውን የተዛቡ ግንኙነቶች በማረም አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሠብ መገንባት ይጠበቅብናል አሉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ ይህንን ያሉት ከአስተዳደር ወሰን፣ ማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ችግሮችና ዘላቂ መፍትሄን በተመለከተ ሲምፖዚየም እየተካሄደ በሚገኝ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
ውይይቱ ሳይንሳዊ ምክረ ሃሳብ ለአስተዳደር ወሰን ፣ማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ችግሮችና ዘላቂ መፍትሄን በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
በስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን ፣ የክልል አፈ ጉባኤዎች ፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
በዚህ ሲምፖዚየም ከአስተዳደር ወሰን ፣ ማንነት እና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር በተያያዘ በሚነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል።
የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ሲምዚየም ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ነው።
በለይኩም ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን