የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርጫፍ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርጫፍ በአዲስ መልክ በማደራጀት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
ቅርጫፉ ቀደም ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር ጉርድ ሾላ ቅርጫፍ በሚል ስያሜ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን÷ በአሁን ወቅት የለሚ ኮራ ቅርጫፍ በሚል ተቀይሮ ነው አገልግሎት መሥጠት የጀመረው።
የቅርጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አስፋው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገተጹት÷ ቅርንጫፉ በሰው ሀይል 90 በመቶ በማደራጀት ስራ መጀመራቸውን ነው የገለጹት ።
በዚህም ቅርንጫፉ የውሀ ስርጭት ዝርጋታ ፣ ውዝፍ ክፍያ፣ቆጣሪ ንባብና ሌሎችንም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ነው ያሉት
ቀደም ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር የነበሩ ወረዳ 8 ፣9 ፣10 ፣ 11 እና 15 በዚሁ ቅርጫፍ ስር መካተታቸውን አመላክተዋል።
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!