Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለምአቀፍ ጥምረት 2 ነጥብ 2 ሚሊየን መጠን የያዘ የኮቪድ 19 ክትባት ተረከበች፡፡

የመጀመሪያው የኮቪድ 19 ክትባት ማለዳ ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ክትባቱ አስትራዜኒካ የተሰኘው መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

የጤና ሚኒስቴርም ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክትባት ፕሮግራሙም በቀጣዮቹ ሳምንታት ይፋ እንደሚደረግም የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.