Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ዜጎች የሀብት ድጋፍ አሰባሰብ ስራ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ዜጎች የሀብት ድጋፍ አሰባሰብ ስራ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በትግራይ ክልል ጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በጁንታው የጥፋት ሀይል የደረሰውን ጥቃት በመመከት እና ህግ እና ስርአት የማስከበሩ ተግባር መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም የጁንታው ሃይል ያደረሰውን ውድመት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ የድሬዳዋ አስተዳደር 5 ሚሊየን ብር ከበጀቱ በመቀነስ ለዚሁ ተግባር እንዲውል መመደቡ ተገልጿል፡፡

በዚህም ድጋፉን በማጠናከርም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከባለሃብቶች፣ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞችና ተቋማት ሃብት ለማሳባሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱንም ከከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.