Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ በስድስት ወራት ውስጥ ከ83 ቢሊየን በላይ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰበ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት አመት 83 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ፡፡

በግማሽ ዓመቱ ባንኩ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን አዳዲስ የተቀማጭ ሂሳቦችን ያስከፈተ ሲሆን÷ የዕቅዱን 221 በመቶ በማከናወን ተጨማሪ 83 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሊያሰባስብ ችሏል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 678 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን÷ ይህም ከዕቅድ በላይ የ107 በመቶ ክንውን ማሳየጡ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የባንኩ ደንበኞች ቁጥርም 27 ነጥብ 5 ሚሊየን ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ  ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች በግማሽ በጀት አመት ውስጥ 47 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አዲስ ብድር አቅርቧል፡፡

በተመሳሳይ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ውስጥ 26 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ከተበዳሪዎች መሰብሰብ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ለተለያዩ የመንግስትና የግል የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና ለገቢና ወጪ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማሰባሰብ በግማሽ በጀት አመቱ የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር አቅርቦት አድርጓል፡፡

እስከ በጀት ዓመቱ ግማሽ ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብት 903 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መድረሱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.