በውሃ ስፖርቶች ሲሰጥ የቆየው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከኦሮሚያ ውሃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከጥር 26 እስከ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ. ም በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ሲሆን 24 ወንዶች እና 2 ሴቶች መሳተፋቸውም ነው የተገለጸው።
የስልጠናው አላማ በአገር አቀፍ ደረጀ ያለውን የባለሙያዎችን እጥረት ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀልቤሳ ኤባ ገልጸዋል ።
አያይዘውም በውሃ ስፖርቶች የዳኝነት እና የአሰልጣኝነት ስልጠና በሌሎች ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
ከዚያም ባለፈ ፌዴሬሽኑ ከየካቲት 20 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት ዓመታዊ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የውሃ ስፖርቶች ሻምፒዮና እንደሚያካሄድ የጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ቀልቤሳ ተናግረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.Fana
በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡