በመዲናዋ ለህብረተሰቡ እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድረ-ገፅ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድረ ገፅ ይፋ ሆነ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክና የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት እንዲያገኝ ያስችለዋል።
በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛውም የገበያ ስፍራ ምርቶች የሚሸጡበትን ዋጋ ባለበት ሆኖ ለማወቅ እንደሚያስችለውም ኃላፊው ገልጸዋል ።
“www.aaminfo.gov.et “በሚል ይፋ የተደረገው የመረጃ ድረ ገጽ ከ28 በላይ የገበያ ማዕከላት ጋር የተሳሰረ መሆኑን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የመረጃ ሥርዓቱ በአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ በትብብር የተዘጋጀ ነው::
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!