Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማሟላት ለአምራቾች የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎች ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማሟላት ለሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠናቸውን እንዲጨምሩ የውጭ ምንዛሬ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲያገኙ በማድረግ እና የድጋፍ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ከሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው በሚያመርቱበትና ምርቱ ፍትሐዊና ተደራሽ ሆኖ በሚሰራጭበት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም መንግስት ለሲሚንቶ አቅራቢዎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሲሚንቶ ስርጭት ስራው ፍትሐዊና ተደራሽ እንዲሆንም የክትትልና ቁጥጥር ስራው ከአምራች እስከ ቸርቻሪ ድረስ ያለው ተዋናይ በጥብቅ ስነ ምግባር እንዲሰራ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ በሙሉ አቅማቸው አምርተው የዘርፉ የፍላጎትና አቅርቦት ልዩነቱ እስከሚሻሻል ድረስ ምርቱ ከውጭ እንዲገባ በማድረግ የሀገሪቱ የግንባታ ዘርፍ በታሰበው ልክ እንዲቀጥልና ዘርፉ የሚፈጥረውን የስራ ዕድል አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.