Fana: At a Speed of Life!

ሐድያ ሆሳዕና የዕግድ ውሳኔ ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐድያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ክለብ ከዚህ በፊት የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጉ ምክንያት የዕግድ ውሳኔ ማስተላለፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የሐድያ ሆሳዕና ተጫዋች የሆነው አብዱልሰሚድ አሊ ደሞዝ አልተከፈለኝም በማለት ያቀረበውን ክስ ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ለተጫዋቹ ደመወዙ እንዲከፈለው ውሳኔ ማሳለፉን ይታወሳል።

ኮሚቴው ለተጫዋቹ ደመወዙ እንዲከፈለው በማለት ውሳኔ ቢያስተላልፍም ክለቡ ግን ይህን ተግባራዊ ባለማድረጉ በቀረበበት አቤቱታ ፌዴሬሽኑ ሐድያ ሆሳዕናን ከማንኛውም አገልግሎቶች የታገደ መሆኑን በደብዳቤ ማስታወቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል።

በዘንድሮው ዓመት በሁሉም መልኩ ተሽሎ የመጣው ሐድያ ሆሳዕና በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ለዋንጫ የሚገመት ቡድን ሆኖ ቀርቦ ነበር።
በቀጣዮቹ ቀናት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕረፍት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ክለቡ ክፍያውን ለተጨዋቹ የሚፈፅም ከሆነ ወደ ውድድር ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.